1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት በኤርትራ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 13 2012

ፕሬዝደንት ኢሳያስ  አፍወርቂ የፋሲካን በዓልንና የረመዳን ፆም መግቢያን ምክንያት በማድረግ ለሐገሪቱ ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት የኮረና ተሕዋሲ ወረርሽኝን "ያልተገመተ ድንገተኛ ጦርነት" ብለዉታል

https://p.dw.com/p/3bE37
Eritrea Straßenszene in Asmara
ምስል Reuters/T. Mukoya

የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት በኤርትራ

 

ኤርትራ ዉስጥ በኮሮና ተሕዋሲ የተለከፈዉ ሰዉ ቁጥር   39 ደርሷል፡፡የኤርትራ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀቁ እስካሁን ድረስ በተሕዋሲዉ ከተለከፉ ሰዎች 3ቱ ተሽሏቸዋል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ  አፍወርቂ የፋሲካ በዓልንና የረመዳን ፆም መግቢያን ምክንያት በማድረግ ለሐገሪቱ ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት የኮረና ተሕዋሲ ወረርሽኝን "ያልተገመተ ድንገተኛ ጦርነት" ብለዉታል።ፕሬዝደንቱ ለሕዝባቸዉ አክለዉ ባስተላለፉት መልዕክት ተሕዋሲን መከላከያዉ ብቸኛዉ ብልሐት "ባለህበት መቆየት ነው» በማለት አስጠንቅቀዋል።ኤርትራ የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን ለመከላከል ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን በረራዎች ዘግታለች፤ በሀገር ውስጥም ከቦታ፣ ቦታ የሚደረግ እንቅስቃሴን አግዳለች፣ትምህርት ቤቶችና የንግድ ተቋማትም ዘግታለች፡፡

 ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ