1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

የኮሮና ተህዋሲ ስርጭት በትምህርት ላይ ያጠላው ስጋት

ቅዳሜ፣ መስከረም 30 2013

በኦሮሚያ ክልል ከጥቅምት 15 ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 15 ባለው ጊዜ በሶስት ምዕራፎች ትምህርት ለማስጀመር ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/3jjuw
Äthiopien Oromia Schule
ምስል S. Getu/DW

ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም ተዋህሲው እምብዛም አልተሰራጨባቸውም ተብሎ በሚታመኑ የወረዳ እና ከዚያ በታች ባሉ መዋቅሮች ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በመጀመሪያ ዙር ከጥቅምት 15 ጀምሮ ትምህርት የሚጀመርባቸው ናቸው ተብሏል የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ፡፡
በወርሃ ጥቅምት ማገባደጂያ ላይ በዞን ደረጃ ባሉ ከተሞች ትምህርት ለመጀመር ሲወጠን ከፍተኛ የተዋሲው ስርጭት ባለባት አዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች ደግሞ ህዳር 15 የትምህርት ማስጀመሪያ ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦለታል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) እና ባለድርሻ አካላት በኦሮሚያ በውስን አከባቢዎች ባደረገው የትምህርት ዝግጅት ምልከታ በዓለም ጤና ድርጅት በተቀመጠው ምክረ ሃሳብ መሰረት በየክፍሎቹ 25 ተማሪዎችን ብቻ ለማስተናገድ የወንበርና የመምህራን እጥረት ፈተና እንዳይሆን አስግቷል፡፡
በኦሮሚያ የፀጥታ ስጋት ያለባቸው አከባቢዎች መኖራቸው ቢጠቆምም ያ ለትምህርት ስጋት የሚሆንበት ደረጃ ላይ አይደለም ያሉት የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ በመላው የክልሉ አከባቢዎች ትምህርት የማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ነው የገለጹት።


ስዩም ጌቱ

ልደት አበበ