የኮሮና ስርጭት ያሰጋዉ ሳዉዲ አረብያ እና ኢትዮጵያዉያን
ማክሰኞ፣ መጋቢት 22 2012ማስታወቂያ
በመካከለኛዉ ምሽራቅ በሳዉዲ አረብያ በኮሮና ተኅዋሲ የተያዘዉ ሰዉ ቁጥር እየጨመረ መሄዱ እየተነገረ ነዉ። መንግሥት ይፋ እንዳደረገዉ እስካሁን ከአንድ ሺ አምስት መቶ በላይ በተኅዋሲዉ የተያዙ ታማሚዎች ተመዝግበዋል። ሦስት ሰዎች ሞተዋል። ከህመም ያገገሙ ደግሞ 66 ሰዎችም እንዳሉ ይፋ ሆንዋል። በሳዉዲ አረብያ ሰዎች በመስጊዶች አካባቢ ሰዎች እንዳይሰበሰቡ ጥብቅ ቁጥጥርም እያካሄደ ነዉ፤ የሰዓት እላፊም ደንግጎአል።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ