የኬሪ ጉብኝትና ኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 18 2008ማስታወቂያ
የዩናይድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ባለፈዉ ሰኞ ናይሮቢ-ኬንያ ዉስጥ የተለያዩ የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮችን ሲያነጋግሩ ኢትዮጵያ በንግግሩ ላይ ሥለመካፈል አለመካፈሏ በግልፅ የተባለ ነገር የለም።የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትም ኢትዮጵያ በዉይይቱ እንድትሳተፍ ተጋብዛ ነበር ከማለት ሌላ ዝርዝር መግለጫ መስጠቱን አልፈለገም።ኬሪ በናይሮቢ ቆይታቸዉ ዩናይትድ ስቴትስ ለደቡብ ሱዳን፤ ለሶማሊያ እና ለኬንያ ጠቀም ያለ ርዳታ እንደምትሰጥ ሲያስታዉቁም የኢትዮጵያ ስም አልተጠቀሰም።የዋሽግተን ዲሲዉ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ጉዳዩን ተከታትሎ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ