የካንኩን የአየር ንብረት ጉባኤ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 21 2003ማስታወቂያ
በዚህ ጉባኤ ላይ ወደሁለት መቶ ከሚሆኑ አገራት የተዉጣጡ ሃያ አምስት ሺ ገደማ ተሳታፊዎች ናቸዉ የሚገኙት። ምንም እንኳን አምና በተስፋ ተጠብቆ እንደታሰበዉ ያልተጠናቀቀዉ ዴንማርክ ኮፐንሃገን ላይ የተካሄደዉ ጉባኤ ጥሩ ያልሆነ ስሜትን ቢጭንበትም ዘንድሮ ቢያንስ ለሚቀጥለዉ ዓመት ጉባኤ መንደርደሪያ የሚሆን ተገቢ መስመር ያስይዛል ተብሎ ይገመታል። የሚቀጥለዉ ዓመት የዚህ ጉባኤ አስተናጋጅ አፍሪቃዊቷ አገር ደቡብ አፍሪቃ ትሆናለች።
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ