የካናዳ መንግሥት የሰጠዉ ማስጠንቀቂያ
ዓርብ፣ ነሐሴ 19 2009ማስታወቂያ
በዚሁ መሠረትም ወደ ኤርትራ፤ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ሶማሊያ አዋሳኝ የድንበር አካባቢ ፈፅሞ እንዳይሄዱ ሲያስጠነቅቅ፤ ወደ ኬንያ የድንበር አካባቢ እና ኗሪዎች ከፀጥታ ኃይላት ጋር ያላቋረጠ ግጭት ዉስጥ ናቸዉ ወዳለዉ ወደ ሰሜን ጎንደር ደግሞ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ ዜጎቹ እንዳይሄዱ አሳስቧል። ዜጎቹ እንዳይሄዱ ያሳሰበበትን አካባቢ በተናጠል በመዉሰድም አሉ ስላላቸዉ የፀጥታ ስጋቶችም ዘርዝሯል። ይህን ማሳሰቢያ አልፈዉ የሚሄዱ የካናዳ ዜጎችም ኃላፊነቱ የራሳቸዉ እንደሚሆን አጥብቆ አሳስቧል። ከቶሮንቶ ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽን ስለጉዳዩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
አክመል ነጋሽ /ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ