የካራቺች መያዝ ያስከተለው ድጋፍና ተቃውሞ15 ሐምሌ 2000ማክሰኞ፣ ሐምሌ 15 2000የካራቺች በፀጥታ ኃይሎች እጅ መውደቅ ለቦስኒያ ሙስሊሞች እና ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብና እንዲሁም ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አስደሳች ዜና ሲሆን እንደ ጀግና ለሚቆጥሯቸው በርካታ ሰርቦች ግን ኢፍትሀዊ ተደርጎ ነው የታየው ።https://p.dw.com/p/Ehugካራዲችና ሚላዲች በስልጣን ዘመናቸው ወቅትምስል APማስታወቂያሶስት ዓመት ተኩል በወሰደው የቦስኒያው ጦርነት በዋና ከተማይቱ በሳራዬቮ ለረገፈው ቁጥሩ ወደ አስር ሺህ ለሚጠጋ ህዝብ ካራዲችንና የዚያን ጊዜውን የጦር አዛዥ ሚላዲችን ዓለም ዓቀፉ ችሎት ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ።