1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከፋ ረሃብ አደጋ በትግራይ

ሰኞ፣ ኅዳር 17 2016

በትግራይ አበርገለ የጭላ ወረዳ ብቻ 46 ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸው ተገለፀ። በወረዳው ካለፈው ዓመት ወዲህ ዝናብ ባለመዝነቡና በሌሎች ምክንያቶች ከፍተኛ ረሃብ ተከስቷል። ባሉት 5 ወራት ብቻ በትግራይ አበርገለ የጭላ ወረዳ 46 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሲሞቱ ሌሎች ከ95 ሺህ በላይ ደግሞ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸው ገልጿል።

https://p.dw.com/p/4ZUay
በትግራይ ክልል በአጠቃላይ ከ5 ሚልዮን በላይ ዜጎች የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ
የከፋ ረሃብ አደጋ በትግራይ ምስል Million Haileselassie/DW

በትግራይ አበርገለ የጭላ ወረዳ 46 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሲሞቱ ሌሎች ከ95 ሺህ በላይ ደግሞ ከፍተኛ አደጋ ላይ ናቸዉ

ባለፊት 5 ወራት በትግራይ ክልል አንድ ወረዳ ብቻ 46 ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸው ተገለፀ። በትግራይ አበርገለ የጭላ ወረዳ ብቻ 46 ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸው ተገለፀ። የወረዳው አስተዳደር እንዳስታወቀው በወረዳው ካለፈው ዓመት ወዲህ ዝናብ ባለመዝነቡና በሌሎች ምክንያቶች ከፍተኛ ረሃብ ተከስቶ ይገኛል ያለ ሲሆን፥ ከሐምሌ ወር 2014 ዓመተምህረት ወዲህ ባሉት 5 ወራት ብቻ በትግራይ አበርገለ የጭላ ወረዳ 46 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሲሞቱ ሌሎች ከ95 ሺህ በላይ ደግሞ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸው ገልጿል።

ባለፈው ክረምት በቂ ዝናብ ባላገኙ የትግራይ አካባቢዎች ላይ ከአሁኑ ረሃብ ጨምሮ ከፍተኛ ማሕበራዊ ቀውስ በስፋት መታየት ጀምሯል። በተለይም በክልሉ አበርገለ የጭላ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ ስዎች ለረሃብ መጋለጣቸው የተገለፀ ሲሆን በወረዳዋ ብቻ ካለፈው ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓመተምህረት ወዲህ ባሉት አምስት ገደማ ወራት 46 ሰዎች በረሃብ መሞታቸው ተገልጿል።

 ድርቅ በትግራይ

የዝናብ እጥረት

በትግራይ ክልል የአበርገለ የጭላ ወረዳ የኢኮኖሚ ዘርፍ ሐላፊ አቶ አለማየሁ ገብረማርያም ለዶቼቬለ እንዳሉት በአካባቢው ለረዥም ግዜ ዝናብ መጥፋቱ እና የሰብል ተባይ በስፋት መከሰቱ በወረዳው የከፋ ረሀብ እንዲከሰት ብሎም በርካቶች እንዲሞቱ ምክንያት መሆኑ አንስተዋል። በአካባቢው የሚገኝ ህዝብ ለመጨረሻ ግዜ የምግብ እርዳታ ያገኘው ባለፈው ዓመት ጥር ወር እንደነበረም ተገልጿል።

ከአበርገለ የጭላ ወረዳ ውጭ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ረሃብ በስፋት እንደሚታይ የሚገለፅ ሲሆን፥ በመቐለ እና ሌሎች ከተሞች እንደሚስተዋለውም በርካታ ከትግራይ የገጠር አካባቢዎች የተሰደዱ አዛውንቶች፣ እናቶች እና ህፃናት በጎዳናዎች በልመና ተሰማርተው ይታያሉ።

 

በትግራይ ክልል በአጠቃላይ ከ5 ሚልዮን በላይ ዜጎች የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ
የከፋ ረሃብ አደጋ በትግራይ ምስል Million Haileselassie/DW

የህፃናት እና እናቶች ኑሮ

ድርቅ እና ረሃብ በከፋ ሁኔታ ባጠቃት የትግራይ ክልል አበርገለ የጭላ ወረዳ፥ በረሃብ ምክንያት የተለያዩ ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች ከመስተጓጎላቸው በተጨማሪ ከ4 ሺህ በላይ ህፃናት ተማሪዎችም ከትምህርት ገበታ መራቃቸው ተነግሯል። ከስፍራው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች እንደሚሉት በአበርገለ የጭላ ወረዳ በተለይም የህፃናት እና እናቶች ኑሮ የከፋ ሆንዋል። አስተያየታቸው የሰጡትን አቶ ሃይለ ሓዱሽ "ሕብረተሰቡ ቤቱ ትቶ እየተፈናቀለ ነው። ከገጠር ወደ ከተማ ፍሰቱ ጨምሯል። ሰዎች እንደቤተሰብ ናቸው እየተሰደዱ ያሉት" ብለዋል።

ትግራይ ክልል በረሐብ ሰዎች እየሞቱ ነው

በትግራይ ክልል በአጠቃላይ ከ5 ሚልዮን በላይ ዜጎች የምግብ እርዳታ እንደሚፈልጉ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ይገልፃል። ዓለምአቀፍ ለጋሾች ለክልሉ በአጠቃላይ ደግሞ ለኢትዮጵያ ያቀርቡት የነበረ የምግብ እርዳታ ለረዥም ወራት ተቋርጦ መቆየቱ ደግሞ በጦርነቱ ምክንያት ተፈጥሮ የነበረው ሰብአዊ ቀውስ ተባብሶ እንዲቀጥል እንዳደረገው ተነግሯል። የአሜሪካው ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤአይዲ እና የዓለም ምግብ ድርጅት ተዘርፏል በማለት አቋርጠውት የነበረ የምግብ እርዳታ አቅርቦት ዳግም እንደሚቀጥሉ ያስታወቁት በያዝነው ወር ነው። በዚሁ ጉዳይ ዙርያ ከክልሉ እና የፌደራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ