የኦፌኮ ባለሥልጣናት የክስ ሂደት
ረቡዕ፣ ግንቦት 3 2008ማስታወቂያ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ነኛ ወንጀል ችሎት በጉርሜሳ አያና መዝገብ የተከሰሱት እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ በቀለ ገርባ የሚገኙባቸው ተከሳሾች ከጠበቆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ዛሬ ትዕዛዝ አስተላለፈ ። ችሎቱ ትዕዛዙን ያስተላለፈው ተከሳሾቹ በሌሉበት ነው ። የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት 22ቱ ተከሳሾች ዛሬ ፍርድ ቤት ያልቀረቡበትን ምክንያት እንዲገለፅም ችሎቱ አዟል ። ተከሳሾች የመቃወሚያ ሃሳባቸውን እንዲያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ሂደቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዘገባ አለው ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ