የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ወደ ኣገር ቤት ለመግባት መወሰኑ6 ጥር 2006ማክሰኞ፣ ጥር 6 2006የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በእንግሊዝኛ ምህጻሩ «ኦ ዲ ኤፍ» ወደ ኣገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰኑን ኣስታወቀ። የግንባሩ ፕሬዝደንት አቶ ሌንጮ ለታ እንደገለጹት ግንባሩ ከምስረታው ኣንስቶ ወደ ኣገር ቤት ለመመለስ ግልጽ አቐም ይዟል።https://p.dw.com/p/1AqNhማስታወቂያ ለኢትዮጵያ ህዝቦች አዲስ ራዕይ ኣለኝ የሚለው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ህጋዊ መሰረት ያለው ኣገራዊ ኣንድነትን ለመመስረት እንደሚሰራም ኣስታውቐል። «ኦ ዲ ኤፍ» በይፋ ከተመሰረተ ገና ኣንድ ዓመቱ ሲሆን ፕሬዝደንቱ አቶ ሌንጮ ለታ ለረጅም ጊዜ የዓማጺው ኦሮሞ ነጻነት ግንብር ከፍተኛ ዓመራር አባል እንደነበሩ ኣይዘነጋም። ጃፈር ዓሊ ነጋሽ ሞሓመድ