የእንስሳት ምርመራ አገልግሎት ቤተ-ሙከራ በሰበታ
ሐሙስ፣ የካቲት 24 2008ማስታወቂያ
የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ምርምር እና ጥናት ማዕከል በሪፈራል ደረጃ ከኢትዮጵያም አልፎ ለመላው የምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት የእንስሳት ምርመራ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጧል። በአርብቶ አደሮች አካባቢ ይታያል ያሉትን የበጎች እና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ለመቆጣጠር ቤተ-ሙከራው አስተዋፅዖው ከፍተኛ መሆኑን የተቋሙ ዳይሬክተር ዶክተር መሥፍን ሣኅሌ ጠቅሰዋል። ማዕከሉ ቀደምስ ሲል ከምሥራቅ አፍሪቃ 11 ሃገራት ለመጡ 24 ሠልጣኞች ለአምስት ወራት የአቅም ግንባታ ሥራ ለመሥራት ሥልጠና መስጠቱም ተገልጧል።
ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ