የእስራኤል ውሳኔ ና አፍሪቃውያን ስደተኞችና
ሐሙስ፣ ጥር 15 2006ማስታወቂያ
በፈቃደኝነት ወደ ሃገራቸው ለሚመለሱም የገንዘብ ማበረታታዎች ይሰጣቸዋል ። በአዲሱ የሆሎት መጠለያ እስከ ጥር ማብቂያ ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ስደተኞቹ በመጠለያው በሚቆዩበት ወቅት ተገን የጠየቁበት ማመልከቻ ይታያል ፤ የሚስጠጉዋቸው ሌሎች ሃገራትም ይፈለጉላቸዋል ። ስደተኞቹ ከመጠለያው መውጣትም ሆነ መግባት ቢፈቀድላቸውም በቀን የተወሰነ ጊዜ መፈረምና እዚያ ማደር ግዴታቸው ነው ። ስለ አጠቃላዩ ሁኔታ የሃይፋውን ዘጋቢያችንን ግርማ አሻግሬን በስልክ አነጋግረነዋል ።
ግርማው አሻግሬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ