የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባዔ መከሰስ
ሐሙስ፣ ጥር 2 2005ማስታወቂያ
በአሸባሪነት ተጠርጥረው እሥር ቤት የሚገኙትና ፣ በዚያ ሆነው ጉዳያቸውን በመከታተል የሚገኙት ፣ የእሥልምና ጉዳዮች መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኘውን የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባዔ (መጅሊስ)እንዲሁም የዑላማዎችን ም/ቤት መክሰሳቸውን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል። አሁን በአመራር ላይ ያለው መጅሊስ ፤ በዛ ያሉ ሙስሊሞች ተቃውሞ ቢያሰሙም ፣ ባለፈው መስከረም 27,2005 ምርጫ ከተካሄደ በኋላ የተሰየመ መሆኑ የታወቀ ነው።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ