1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ ወደ ኢጋድ መድረክ መመለስ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 6 2015

"መልካም አንድምታ አለው ብዬ ነው የማስበው። እንደሚታወቀው በአካባቢው ውጥረቶች አሉ። እንደአጠቃለይ አካባቢውን ከማረጋጋት አንጻር አወንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብዩ ነው የማምነው።"

https://p.dw.com/p/4SWsL
IGAD Logo

የኤርትራ ወደ ኢጋድ መድረክ መመለስ

ኤርትራ ከ16 ዓመታት በኋላ ወደ የምሥራቅ አፍሪቃ በይነመንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ መድረክ መመለሷ የአካባቢው ሐገራት ትብብርን እንደሚያጎለብት የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪዎችና ተንታኞች ተናገሩ። ምሁራኑ እንዳሉት የኤርትራ መመለስ ለራሷም ሆነ ከአካባቢ ሐገሮች ያሉባትን ችግሮች ተቀራርቦ ለመስራት ይጠቅማታል።

ኤርትራ ከ16 ዓመታት ከኢጋር መድረክ መገለል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኞ ዕለት በጅቡቲ በተካሄደው ስብሰባ ተካፍላለች። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ኤርትራ ተመልሳ ወንበሯን መረከቧንና ለአካባቢው ሰላም፣ጸጥታና ውህደት እንደምትሰራ በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል። ይህን ጉዳይ እንዴት ተመለከታችሁት ስንል የፖለቲካ እና የውጭ ግኑኝነት ምሁራንን አነጋግረናል። ዶክተር ጌድኦን ገሞራ ኢጋድን ጭምር በማማከር የሚታወቀው አለምአቀፍ የልህቀት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ

 "መልካም አንድምታ አለው ብዬ ነው የማስበው። እንደሚታወቀው በአካባቢው ውጥረቶች አሉ። እንደአጠቃለይ አካባቢውን ከማረጋጋት አንጻር አወንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብዩ ነው የማምነው።"

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪና መምህር ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖም የዶክተር ጌድኦን ሐሳብ ይጋራሉ።

"ኤርትራ መመለሷ ለራሷ ለኤርትራም ጥሩ ይመስለኛል። ምክንያቱም ከአካባቢው ሐገሮች ጋር በምክክርና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጉዳዮች እንዲያልቁ ጥሩ አጋጣሚ የሚፈጥር ነው። በሌላም መልኩ ኤርትራ ከኢጋድ ውጭ መሆኗ ለአካባቢው ሐገሮች ምቾት የሚሰጥ አልነበረም።.ስለዚህ ተቀራርቦ ለመስራት ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ። "

Äthiopien | IGAD
ምስል Solomon Muchie/DW

ሌላው ያነጋገርናቸው  ከውጭ ጉዳዮች ምርምር ኢኒስቲቱት ዶክተር ወርቁ ያዕቆብ ናቸው።

"የምስራቅ አፍርቃ ብዙውን ጊዜ በጦርነት እና በድርቅ ነው የሚታወቀው። ለዚህም አስተዋጽኦ ያደረገው ተቀራርቦ አለመስራት ነው። ኡርትራ አሁን አባል ሆና መምጣቷ በቀጠናው ያሉ ሐገራት በጋራ ጉዳይ ላይ ተናቦ ለመስራት ያስችላል።"

ኤርትራ ከኢጋድ መድረክ ለመታገዷ በወቅቱ የነበረው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በምክንያትነት ይጠቀሳል። አሁን በህወሐትና በፌደራል መንግስት በተካሄደ ጦርነትም ኤርትራ ትግራይ ውስጥ በመግባት በርካታ ግፍ መፈጸሟንና አሁንም ድረስ ሰራዊቷን ከትግራይ አለማስወጣቷን የአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ ያመላክታል። የኤርትራ ወደ ኢጋድ መድረክ መመለስ አሁንም ለሚነሱ ችግሮች በውይይት ለመፍታት እንደሚያግዝ ነው ዶክተር ጌድኦን የሚያምኑት።

የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ኤርትራን እንኳን በደህና መጣሽ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

 ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር

ታምራት ዲንሳ