የኤርትራና የትግራይ እሰጥ አገባ
ረቡዕ፣ የካቲት 4 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ይገባኛልና ሌሎች ውዝግቦች በሕግና ስርዓት የመጨረሻ መፍትሔ ሊሰጣቸዉ እንደሚገባ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሊቀመንበርና የትግራይ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አስታወቁ። ሊቀመንበር ደብረፅዮን በቅርቡ የኤርትራዉ ፕሬዝደንት ለሰጡት አስተያየት አፀፋ በመሰለ መግለጫቸው ለየውዝግቡ አብነቱ ሕጋዊ መፍትሔ ማግኘት ነው። የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያና ኤርትራ ሰላም ለማውረድ ከተስማሙ በኋላ የሁለቱ ሐገራት የድንበር ሁኔታን «የከፋ» ብለዉታል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ ለሁኔታው መክፋት የትግራዩን ገዢ ፓርቲ ሕወሓትን ተጠያቂ አድርገዋልም።
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ