የኢጣሊያ አዲስ መንግሥት ምሥረታ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 5 2004ማስታወቂያ
የኢጣሊያ ተመራጭ ጠቅላይ ሚንስትር ማሪዮ ሞንቲ ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት ለመመሥረት ከሐገሪቱ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር የሚያደርጉትን ዉይይት ዛሬም እንደቀጠሉ ነዉ።ሞንቲ ለሚመሠርቱት መንግሥት የሐገሪቱን ትላልቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ አግኝተዋል። የቀድሞዉ የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽነር ማሪዮ ሞንቲ ኢጣሊያ የገጠማትን የምጣኔ ሐብት ኪሳራ ለማስወገድ ይረዳሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል።የመንግሥት ምሥረታዉን ሒደት በተመለከተ ሸዋዬ ለገሠ የሮማ ወኪላችን ተኽለ እግዚ ገብረ የሱስን በስልክ አነጋግራዋለች።
ተኽለ እግዚ ገ/እየሱስ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ