ተቃውሞው ቀጥሏል
ረቡዕ፣ ሐምሌ 19 2009ማስታወቂያ
የእስራኤል መንግስት እየሩሳሌም ወደ ሚገኘዉ የሙስሊሞች ቅዱስ መስጊድ አል አቅሳ ለሶላት የሚገቡ ሰዎችን በብረት መለያ መሳሪያ ለመፈተሽ ተክሎት የነበረዉን መሳሪያ ትናንት አንስቷል።ይሁንና ምዕመናንን የሚቆጣጠርበት የቪዲዮ ካሜራ ግን አሁንም እንዳለ ነዉ።በዚሕም ምክርንያ መፈተሻዉ መሳሪያ ከተተከለ ጀምሮ ፍልስጤሞች የሚያደርጉት ተቃዉሞ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ተቃዉሞና ግጭቱ እንዳይጠናከር እና ወደ ሌላ ሥፍራ እንዳይዛመት የተለያዩ መንግሥታት እና ማሕበራት የሚያደርጉት ጥሪም እንደቀጠለ ነዉ።
ዜናነህ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ