ኢትዮ ቴሌኮም
ሐሙስ፣ ነሐሴ 17 2010ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም በሞባይል ኢንተርኔት፣ በሞባይል የድምጽ ጥሪ እና በሞባይል አጭር የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎቶች ላይ ከትናንት ጀምሮ የአግልግሎት ታሪፍ ቅናሽ አድርጓል። የታሪፍ ቅናሹን ይፋ ያደረጉት የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ፍሬ ህይወት ታምሩ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት የታሪፍ ቅነሳው የብሮድ ባንድ ኢንተርኔት እና የብሮድባንድ ቪ ፒኤን እና ሌሎች አገልግሎቶችንም ያካትታል። ሥራ አስኪያጇ የአሁን የታሪፍ ማሻሻያ ድርጅቱን ወደ ፊት ለግል ባለሀብቶች ለማዛወር ከተያዘው እቅድ እንደማይገናኝ አስረድተዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ