የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ውሎ
ረቡዕ፣ ግንቦት 2 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ዛሬ ሥራ በዝቶባቸው ውሏል። ከ50 በላይ ሰዎች በሞቱበት የኢሬቻ ተቃውሞ እና አደጋ የኢትዮጵያ መንግሥት ክስ የመሰረተባቸው 9 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ። ከሰባት ወራት እስር በኋላ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ግለሰቦች የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ዛሬ ሰጥተዋል። በእነ ቀመር ሐጂ መዝገብ የተካተቱት 9 ሰዎች የሽብር ክስ እንደተመሰረተባቸው ጠበቃቸው ተናግረዋል። የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በአቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀው ችሎት ብያኔ አልደረሰልኝም በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የአቶ ዮናታን ተስፋዬ የክስ ሒደት 1 አመት ከ5 ወር አስቆጥሯል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ