1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ገባ መባሉ

ሰኞ፣ ኅዳር 11 2004

በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች በጦርና በማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ታጅበው ወደ ደቡብና ማዕከላዊው ሶማሊያ መግባታቸውን የዜና ምንጮች እማኞችን በመጥቀስ አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/Rxdn
የኢትዮጵያ ወታደሮች በኪስማዮ -ከ 4 ዓመት በፊትምስል picture-alliance/ dpa

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ትናንት ድንበር ተሻግሮ ሶማሊያ መግባቱን የዜና ምንጮች እየገለፁ ነው። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች በጦርና በማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ታጅበው ወደ ደቡብና ማዕከላዊው ሶማሊያ መግባታቸውን ምንጮቹ እማኞችን በመጥቀስ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ዜናውን እስካሁን አስተባብሏል። ስለሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ ልደት አበበ ሞቃድሾ የሚገኘውን የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ሁሴን አዌይስ አነጋግራዋለች።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ