የኢትዮጵያ ጦር ተመልሶ ሞቃዲሾ ገባ መባሉ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2001ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ከፊል ጦር ከሞቃዲሾ ሲወጣ፤ በአንፃሩ ሌላ ተጨማሪ ጦር ወደ ሞቃዲሾ እየገባ መሆኑን ጋዜጠኛ አብዲ ዋህድ ከሶማሊያ ገለፀ። ለዘብተኛ እስላማዊ ቡድን በሞቃዲሾ ሶስት ፓሊስ ጣቢያዎችን እንደተቆጣጠረ ነው ተብሏል። አህሉ ሱና የተሰኘ አዲስ ቡድን ደግሞ ሰሞኑን ነፍጥ አንስቶ አልሸባብ ከተሰኘው እስላማዊ ቡድን ጋር ውጊያ መጀመሩም ተነግሯል። በዚህም የተነሳ ሶማሊያ ተመልሳ ወደ እርስ በርስ ግጭት እንዳታመራ ነዋሪዋ ሰግቷል።