የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንትስር መልዕክትና ትርጓሜዉ
እሑድ፣ ሰኔ 1 2006ማስታወቂያ
ኢሕዴግ ሥልጣን የያዘበትን ሃያ ሰወስትኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሐይለ ማርያም ደሳለኝ በተከታታይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።የበዓሉ ዕለትም ሠፋ ያለ መርሕ ጠቀስ ንግግር አድርገዋል። እስካሁን በተያዘዉ ዕቅድ መሠረት አምስተኛዉ ብሔራዊ ምርጫ በመጪዉ ዓመት ይደረጋል።የግንቦት ሃያ በዓል የተከበረዉ፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክት የተደመጠዉም የገዢዉ ፓርቲ የኢሕዴግም፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፖለቲከኞች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም ለምርጫ በተዘጋጁበት፤ የፖለቲካ ታዛቢዎች ሥለምርጫዉ ዝግጅት፤ ሥለ የፖለቲካ ማሕበራቱ አቋም በሚተነትኑበት ወቅት ነዉ።በዚሕም ሰበብ የዛሬ ዉይይታችን ጠቅላይ ሚንስትሩ ካስተላለፏቸዉ መልዕክቶች መሐል ሥለ መጪዉ ምርጫና ሥለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተናገሩት ላይ ነዉ የሚያተኩረዉ።
ነጋሽ መሐመድ
ልደት አበበ