የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር 50ኛ ዓመት በዓል
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 29 2011ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር (ኢጋማ) የተመሰተተበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤሊዩ በስካይ ላይት ሆቴል አከበረ። ማኅበሩ ባለፉት የ50 ዓመታት ዕድሜው የጋዜጠኝነት ሞያን ለማጎልበት ጥረት ማድረጉን ጠቅሷል። ኾኖም «በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት እንዲከበር በመታገል በኩል» የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር «ኢጋማ የሚጠበቅበትን ያህል እንዳልሠራ አይካድም» ሲሉ የማኅበሩ ፕሬዚደንት መሠረት አታላይ ተናግረዋል። «ፖለቲከኛ ተጽዕኖዎችን በገለልተኝነት መንፈስ አለመጋፈጡ ኹሌም በቊጭት የምናወሳው የኢጋማ ደካማ ጎን ነው» ብለዋል። በሥፍራው የተገኘው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በሞያው የተሠማሩ የተለያዩ ሰዎችን አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ