የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ይዞታ እና የአዉሮጳ ሕብረት
ማክሰኞ፣ ጥር 3 2008ማስታወቂያ
ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ የሕብረቱ ባለሥልጣናት ሰሞኑን ብራስልስ ዉስጥ ለሚያነጋግሯቸዉ ለኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ለቴዎድሮስ አድሐኖም የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች ሠላማዊ ሠልፈኞችን መግደል፤ ማቁስል ማሰራቸዉን ሕብረቱ እንደሚቃወም በግልፅ መንገር አለባቸዉ።ሒዩማን ራይትስ ዋች እንደሚለዉ የአዉሮጳ ሕብረት «ዝምታዉን ሠብሮ» የኢትዮጵያ መንግሥትን የ«ጭካኔ እርምጃ» ማዉገዝ አለበት።የድርጅቱን የአፍሪቃ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በቀልን በሥልክ አነጋግረነዋል።
ነጋሽ መሃመድ
ሂሩት መለሰ