የኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ
ሐሙስ፣ ኅዳር 17 2013ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል እየተከናወነ ያለውን ሕግ የማስከበር ተግባር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስገንዘብ ረገድ ስኬታማ ሥራ ማከናወኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።
ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በከፍተኛ የልዑካን ቡድን አባላት የተደረጉት የሥራ ጉብኝቶች ሀገራቱ ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ያረጋገጡበት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለዶይቼ ቬለ ገልፀዋል። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲያደርግ ጭምር የተገፋው አጀንዳ አለመሳካት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን ጉዳይ ለመረዳቱ ማሳያ መሆኑንም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።
ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ