1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥሪና የትግራይ አባቶች ምላሽ

ሐሙስ፣ የካቲት 2 2015

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንኙነቱ ዳግም እንዲጀመር የሚጠይቀዉ ደብዳቤ ከደረሳቸዉ አንዱ የዓዲግራት ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁእ አባ መርሐክርስቶስ ዛሬ ለዶቸ ቬለ «የሚቀያየር አቋም የለንም» ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4NIcO
Tigray Orthodox Kirche Bischof
ፎቶ፦ ከማኅደራችን የትግራይ ክልል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሐይማኖት አባቶችምስል Million Haileselasie/DW

«የሚቀያየር አቋም የለንም» ብፁእ አባ መርሐክርስቶስ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጦርነቱ ምክንያት ከትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርስቲያን ጋር የተቋረጠዉ ግንኙነት እንዲቀጥል በደብዳቤ ጠየቃለች። የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ከኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር ግንኙነቱን ማቋረጣቸው ያስታወቁት ባለፈው ዓመት ነበር። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትሪያክ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ የፈረሙበት ግንኙነቱ ዳግም እንዲጀመር  የሚጠይቀዉ ደብዳቤ ከደረሳቸዉ አንዱ የዓዲግራት ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁእ አባ መርሐክርስቶስ ዛሬ ለዶቸ ቬለ «የሚቀያየር አቋም የለንም» ብለዋል።

ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ