1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወዳጅ-ጠላት-ወዳጅ እንደገና-----ኢትዮ-ኤርትራ

ነጋሽ መሐመድ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 20 2016

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ በያዝነዉ ጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ የማንሳት መብት አላት ማለታቸዉ ደግሞ የአዲስ አበባና የአስመራ መሪዎችን ልዩነት ይበልጥ ለማስፋት እንደምክንያት እየተጠቀሰ ነዉ።

https://p.dw.com/p/4YE58
«ቀይ ባሕርን ተወልጄ፣ ያደግሁበት--- ነዉ»
የሱፍ ያሲን፣ የፖለቲካ ተንታኝና ደራሲምስል privat

ከፖለቲካ ተንታኝ የሱፍ ያሲን ጋር የተደረገ ቃለ መጠየቅ

ኢትዮጵያ ዉስጥ ከተከታታይ ሕዝባዊ ትግልና ተቃዉሞ በኋላ መጋቢት 2010 የተደረገዉ የፖለቲካ መሪዎች ለዉጥ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበት ነበር።በዚያዉ ሰሞን ከ20 ዓመት በላይ የቆየዉ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጠብና ወታደራዊ ፍጥጫ አብቅቶ በሁለቱ ሐገራት መካካል ሠላም ማዉረዱ ለሁለቱ ሐገራት ሕዝቦች ትልቅ ተስፋ አሳድሮ ነበር።

የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድና የኤርትራ ፕሬዝደንት የመሰረቱት ስምምነትና ጠንካራ ወዳጅነት ዓለም አቀፍ እዉቅናም አግኝቶ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ የ1919ኙን (እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር) የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል።ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ በተለይ የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት በሰላም ስምምነት ካበቃ በኋላ ግን በሁለቱ መሪዎች በዉጤቱም በሁለቱ ሐገራት መካከል የነበረዉ ወዳጅነት እየተቀዛቀዘ፣ ቦታዉን ለጠብና እስጥ አገባ እየለቀቀ ይመስላል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ በያዝነዉ ጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ የማንሳት መብት አላት ማለታቸዉ ደግሞ የአዲስ አበባና የአስመራ መሪዎችን ልዩነት ይበልጥ ለማስፋት እንደምክንያት እየተጠቀሰ ነዉ።  

ከግራ ወደ ቀኝ ፕሬዝደንት ኢሳያስና ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ እጅ ለእጅ ተያይዘዉ
የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በ2010 አዲስ አበባን ሲጎበኙምስል picture alliance/AP Photo/M. Ayene

አንንዳድ ዘገቦች እንደሚጠቁሙት ደግሞ ሁለቱ ሐገራት ጦራቸዉን በአዋሳኝ ድንበሮች አካባቢ እየሰፈሩ ነዉ።እዉነት ይሆን? አለመግባባቱስ ወዴት ያመራ ይሆን? ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር የወደብ ጥያቄስ ኤርትራ፣ ሶማሊያና ጅቡቲ ያሰሙት ተቃዉሞ ተገቢ ይሆን? የአፍሪቃ ቀንድ የፖለቲካ ተንታኝና ደራሲ የሱፍ ያሲንን አነጋግረናቸዋል።ሙሉ ቃለ መጠየቁን እነሆ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ