«ባለስልጣናቱ መጠየቅ አለባቸዉ» ሁይማን ራይትስ ዋች
ሐሙስ፣ ሰኔ 28 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሶማሌ መስተዳድር ባለሥልጣናት ሰዎችን በዘፈቀደ እያሰሩ አሰቃቂ ግፍ እንደሚፈፅሙባቸዉ ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ሁዩማን ራይትስ ዋች አጋለጠ።የመብት ተሟጋቹ ድርጅት «እኛ ልክ እንደ ሙት ነን» ባለዉ ዘገባዉ እንዳስታወቁ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነ አዉጪ ግንባር (ኦብነግ) አባላት ናችሁ እየተባሉ ኦጋዴን በተባለዉ ወሕኒ ቤት የታሰሩ ተጠርጣሪዎች የሚደርስባቸዉ ግፍ ከልክ ያለፈ ነዉ።የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስት እስረኞችን በሚያሰቃዩ ባለሥልጣናት ላይ እርምጃ እንዲወስድ ሑዩማን ራይትስ ዋች አሳስቧል።የቶሮንቶ ወኪላችን አክመል ነጋሽ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
አክመል ነጋሽ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ