የኢትዮጵያ ምርጫና የምሑራን ጥያቄ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 28 2013ማስታወቂያ
ርዕይ ለኢትዮጵያ የተባለዉ ማሕበር ኢትዮጵያ ዉስጥ በቅርቡ ሊደረግ የታቀደዉ ምርጫ ቀርቶ በአስቸኳይ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ጠየቀ።ዋና መቀመቻዉን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገዉ ማሕበር እንደሚለዉ ኢትዮጵያ «ከባድ» ያለዉ የሕልዉና ስጋት አጋጥሟታል።በተለያዩ ሐገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን ግን ምርጫዉ በተያዘለት ጊዜ እንዲደረግ እየጠየቁ ነዉ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣዉ የጊዜ ሠለዴ መሠረት አምና በኮሮና ተሕዋሲ ሥርጭት ምክንያት የተገፋዉ ብሔራዊ ምርጫ የፊታችን ግንቦት 28 ይደረጋል።
ታሪኩ ኃይሉ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ