የኢትዮጵያ ሙስሊም መሪዎች የፍርድ ሒደት
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 3 2006ማስታወቂያ
ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በነፃ ካሰናበታቸዉ ተከሳሾች መካካል የቀድሞዉ የሲቪል ሠርቪስ ሚንስትር የአቶ ጁኔዲ ሳዶ ባለቤት እና ሁለት ድርጅቶች ይገኙባቸዋል።የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጋ እንደገለፁት ፍርድ ቤቱ በሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ላይ የተያዘዉን የወንጀል ጭብጥም «ከአሸባሪነት» ወደ «ሽብር አነሳሽነት» እና ተባባሪነት አቅልሎላቸዉል።የቀሪዎቹን ጉዳይ ለማየት ፍርድ ቤቱ ለመጪዉ ጥር ሃያ-ሁለት ቀጠሯል። አቶ ተማምን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግሯቸዋል።
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ