የኢትዮጵያ መንግሥት ርምጃና CPJ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 20 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችን ማሠሩን እና መረጃ የማግኘት መብትን መገደቡን እንዲያቆም ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ አስታወቀ።በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ CPJ ተብሎ የሚጠራዉ ኮሚቴ እንዳስታወቀዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባንድ ሳምንት ዉስጥ ሁለት ጋዜጠኞችን አስሯል።በኮሚቴዉ መግለጫ መሠረት የኦሮሚያ ቴሌቪዥን ጣቢያ አዘጋጅ ፈቃዱ ሚርካና እና ነገረ-ኢትዮጵያ የተባለዉ ለተቃዋሚዉ ለሠማዊ ፓርቲ የወገነዉ አምደ መረብ ዋና አዘጋጅ ጌታቸዉ ሽፈራዉ የታሠሩበት ምክንያት ግልፅ አይደለም።የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን ናትናኤል ወልዴ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ናትናኤል ወልዴ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ