የኢትዮጵያ መንግሥትና የአዉሮጳ ሕብረት
ሐሙስ፣ ሐምሌ 24 2006ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችን፤የአምደ-መረብ ፀሐፍትንና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ማሰሩ እንዳሳሰበዉ የአዉሮጳ ሕብረት አስታወቀ።በሕብረቱ የኢትዮጵያ ጉዳይ ልዑክ ባወጣዉ መግለጫ የእስረኞቹ አያያዝ የኢትዮጵያን ሕገ-መንግሥት፤ ዓለም አቀፍና አሐጉራዊ የሠብአዊ መብት ድንጋጋዎችን ያከበረ ለመሆኑ ማረጋገጫ እንዲሰጠዉም አሳስቧል።እስረኞቹ ከቤተ-ሠቦቻቸዉ፤ ከዘመድ ወዳጆቻቸዉ እና ከጠበቆቻቸዉ ጋር እንዲገናኙ፤ የዋስ መብታቸዉ እንዲከበር እና የፍርድ ሒደቱም ግልፅና ነፃ እንዲሆን አሳስቧልም።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ