የኢትዮጵያ መብራት ኃይልና ፕሮጀክቶቹ
ረቡዕ፣ መስከረም 3 2004ማስታወቂያ
ድርጅቱ በመንግሥት የሚገነቡትን ከፍተኛ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ለማሠራት ከ 8 ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች ጋር ባለፈው ሳምንት ስምምነት ተፈራርሟል ። የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ለኃይል ማመንጫ መሰረተ ልማት የሚወጣውን ገንዘብ በማባከንና በብልሹ አሠራር በሃገሪቱ ጠቅላይ ኦዲተር ከዚህ ቀደም ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለዚሁ ዶቼቬለ የጠየቃቸው የመብራት ኃይል ስራ አስኪያጅ አቶ ምህረት ደበበ መስሪያ ቤታቸው ወደፊት ሊያሰራቸው በተፈራረማቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ስህተቶቹን ለማረም እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።ታደሰ እንግዳው
ታደሰ እንግዳው
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ