1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ለአፍሪቃዊ ችግር አፍሪቃዊ መፍትሔ አቋም

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 7 2013

ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ከግብጽ እና ሱዳን ጋር የምታደርገው ድርድር ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔን መሰረት ያደረገ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ግብጽ እና ሱዳን ከአፍሪካ ሕብረት በተጨማሪ ጥቅሞቻቸውን ሊያስጠብቁላቸው የሚችሉ ሌሎች አካላት የህብረቱን ሚና እንዲጋሩ የሚያደርጉትን ጥረት ኢትዮጵያ አትቀበልም ብሏል።

https://p.dw.com/p/3s4vT
Äthiopien Botschafterin Dina Mufti
ምስል Solomon Muchie/DW

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት አቋም

ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ከግብጽ እና ሱዳን ጋር የምታደርገው ድርድር ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔን መሰረት ያደረገ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ በሳምንታዊ መግለጫው እንዳለው ግብጽ እና ሱዳን ከአፍሪካ ሕብረት በተጨማሪ ጥቅሞቻቸውን ሊያስጠብቁላቸው የሚችሉ ሌሎች አካላት የህብረቱን ሚና እንዲጋሩ የሚያደርጉትን ጥረት ኢትዮጵያ አትቀበልም ብሏል። የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይን ጨምሮ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይም የውች ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ዲና ሙፍቲ ዝርዝር መግለጫ ሰጥተዋል። መግለቻውን የተከታተለው ሰለሞን ሙጬ ተከታዩን ዘገባ ከአዲስ አበባ ልኮልናል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ