የኢትዮጵያውያን ስሞታ ከሳዉዲ እሥር ቤት
ሰኞ፣ የካቲት 24 2006ማስታወቂያ
ዘግናኝ እርምጃዎች ከተወሰዱባቸው በኋላ ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ፣ ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ንብረታቸውን በቅጡ ሳይሰበሰቡ ወደ ትውልድ ሃገራቸው መመለሳቸው የሚታወስ ነው። ገሚሱ በተለያዩ ምክንያቶች ገና እንዳልተመለሱ ታውቋል። «የሥራ ፈቀድ የነበረን ነን፣ ሆኖም ፣ መመለስ ፈልገን ከመንግሥት በኩል ትብብር አልተደገልንም በማለት የሚያማርሩ ኢትዮጵያውያን ፣ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ከመደረጉ በፊት ፤ በሳምንቱ ማለቂያ ላይ ፣ ከዚያው ከስዑዲ ዐረቢያ ከጂዳ ፤ እሥር ቤት ከ SMSም ሌላ በስልክ እንዲህ ነው ብሶታቸውን የገለጡልን።
ተክሌ የኋላ
ኂሩት መለሰ