የኢትዮጵያዉያን መንገላታት እና አምባሳደሩ
ዓርብ፣ ሰኔ 30 2009ማስታወቂያ
የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ሕገ-ወጥ ያላቸዉ የዉጪ ዜጎች ከሐገሩ እንዲወጡ በሰጠዉ የጊዜ ገደብ ወደ ሐገራቸዉ መግባት በፈለጉ ኢትዮጵያዉያን ላይ ደርሶ የነበረዉ መንገላታት መቃለሉን በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አሚን አብዱልቃድር አስታወቁ።በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን በሰነድና በመጓጓዣ እጦት መንገላታታቸዉን በተደጋጋሚ ሲገልጡ ነበር።የሳዑዲ አረቢያ መንግስት የጊዜ ገደቡን ባንድ ወር ቢያራዝምም ወደ ሐገራቸዉ መመለስ የፈለጉ ኢትዮጵያዉያን አሁን በመጓጓዢያ እጦት አዉሮፕላን ማረፊያዎች፤በኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አዳራሽና በየሰዉ ቤት ለመጠለል ተገድደዋል።አምባሳደር አሚን ተመላሾች በቀረዉ ጊዜ ዉስጥ ለጉዞ እንዲዘጋጁ መክረዋል።
ስለሺ ሽብሩ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ