1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና ኤርትራውያኑ ተቃውሞ በ CNN መሥሪያ ቤት

ሐሙስ፣ ኅዳር 23 2014

በአትላንታ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የ CNN ጣቢያ በየሃገሮቹ ጉዳይ ላይ ያቀርበዋል ያሉትን የተዛባ ዘገባ አወገዙ። በሲኤንኤን ዋና መሥሪያ ቤት ደጃፍ ላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያኑ ትናንት ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ የባይደን አስተዳደር በየሀገሮቹ ጉዳይ ላይ ያደርገዋል ያሉትን ያልተገባ ጣልቃ ገብነትና ጫናም በፅኑ ተቃውመዋል።

https://p.dw.com/p/43kmS
USA Äthiopische und eritreische US-Amerikaner protestieren in Atlanta, Georgia
ምስል Tariku Hailu/DW

«ሐሰተኛ ዜና ይብቃ»

በአትላንታ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የሲኤንኤን ጣቢያ በየሃገሮቹ ጉዳይ ላይ ያቀርበዋል ያሉትን የተዛባ ዘገባ አወገዙ። በሲኤንኤን ዋና መሥሪያ ቤት ደጃፍ ላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያኑ ትናንት ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ የባይደን አስተዳደር በየሀገሮቹ ጉዳይ ላይ ያደርገዋል ያሉትን ያልተገባ ጣልቃ ገብነትና ጫናም በፅኑ ተቃውመዋል። «ሐሰተኛ ዜና ይብቃ» በሚል መሪ መፈክር የተሰባሰቡ የአትላንታ ከተማ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን፤ ኤርትራውያን፤ ትውልደ ኢትዮፕያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተቃውሟቸውን አስተጋብተዋል። በሲኤንኤን ዋና መሥሪያ ቤት ደጃፍ ላይም ተገኝተው ያሰሙትን ተቃውሞ ከሲኤንኤን በኩል መጥቶ የዘገበ አለያም ያነጋገራቸው አካል አለመኖሩንም ሰልፈኞቹ ተናግረዋል። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫና እያሳደረ ነው ያም በመሆኑ በአሜሪካ ምርጫ ወቅት ዴሞክራቶችን እንቀጣለን ብለዋል። ከዚህ ቀደም በምርጫው ዴሞክራቶች እንዳይመረጡ ማድረጋቸውንም እንደ አብነት አንስተዋል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት በመግባት የሚወራውን ውዥንብርም እንቀለብሳለን ብለዋል። 

ታሪኩ ኃይሉ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ