የኢትዮጲያዊትዋ አሟሟት በቤይሩት
ሐሙስ፣ መጋቢት 6 2004ማስታወቂያ
ቤይሩት ሊባኖስ ውስጥ የራስዋን ህይወት አጠፋች የተባለችው ኢትዮጵያዊት ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል ። በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል አቶ አሳምነው ደበሌ ትናንት ኢትዮጵያዊቷ የተኛችበት ሆስፒታል ሲሄዱ ህይወቷን እንዳጠፋች እንደተነገራቸው ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። የኢትዮጵያዊቷን ጉዳይ የሚከታትሉ በዚያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ማሀበረሰብ እባላት ግን አሟሟቷ መታወቅ መጣራት አለበት ይላሉ ። ሁለቱን ወገኖች ያነጋገረው የጂዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ነብዩ ሲራክ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ