የኢሳያስ እና የቢን ዘይድ ዉይይት
ማክሰኞ፣ ሰኔ 26 2010ማስታወቂያ
የኤርትራዉ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አልጋወራሽ ከልዑል ሼሕ መሐመድ ቢን ዘይድ ጋር ዛሬ ዱባይ ዉጥት ተገኛኝተዉ ተወያዩ።ፕሬዝደንት ኢሳያስ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ለመጎብኘት አቡዳቢ የገቡት ትናንት ነዉ።የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በቲዊተር ገፃቸዉ እንደፃፉት ሁለቱ መሪዎች የኤርትራን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል። ሁለቱ መሪዎች በቅርቡ የተከሰቱ ዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በየሐገራቱ ሥለሚኖረዉ ትርጉም አንስተዉ መክረዋል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የ20 ዓመት ጠባቸዉን ለማብረድ በቅርቡ ተስማምተዋል።የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ በቅርቡ ፊትለፊት ተገናኛተዉ ለመወያየት ቀጠሮ አላቸዉ።ለሁለቱ ሐገራት መቀራረብ የሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መሪዎች አስተዋፅኦ ማድረጋቸዉ በሰፊዉ ይታመናል።
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ