የኢሮብ ሕዝብ ተቃዉሞ
ዓርብ፣ ሰኔ 1 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ፤ የኢትዮጵያ ኤርትራን የድንበር ዉዝግብ ያስወግዳል ተብሎ የነበረዉን ሥምምነት እና ዉሳኔን ገቢር እንደሚያደርግ ማስታወቁን የምሥራቅ ትግራይ ኢሮብ ወረዳ ነዋሪዎች ተቃወሙት።የኢሕአዴግ ሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈዉ ማክሰኞ ባሣለፈዉ ዉሳኔ መሠረት ኢትዮጵያ የኢትዮ-ኤርትራን የሠላም ዉል እና የድንበር አካላይ ኮሚሽኑን ዉሳኔ ገቢር ታደርጋለች። ዛሬ ደሐን በተባለች ከተማ የተሰለፉት የኢሮብ ብሔረሰብ አባላት እንደሚሉት ግን ዉሳኔዉ የኢሮብን ሕዝብ ለሁለት የሚከፍል በመሆኑ አይቀበሉትም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለስ