ኢህአዴግ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች
ዓርብ፣ የካቲት 24 2009ማስታወቂያ
ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ለድርድር የተቀመጡት ኢህአዴግ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በድርድሩ ዓላማዎች ላይ መግባባት ላይ ደረሱ ። በውይይቱ የተካፈሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ሁለቱ ወገኖች 5 ነጥቦችን በያዘው የድርድሩ ዓላማዎች ላይ ተስማምተዋል ።ይሁን እና የመነጋገሪያ ሰነዱ ርዕስ ላይ ገና አልተስማሙም ። ድርድሩ በሚቀጥለው ሳምንትም እንደሚቀጥል የአዲስ አበባው ወኪላችችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ