የአፍጋኒስታኑ ጦርነት የአሜሪካዊዉ ዲፕሎማት ተቃዉሞ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 19 2002ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ አፍቃኒስታን ዉስጥ የምታደርገዉን ጦርነት በመቃወም አንድ የሐገሪቱ ዲፕሎማት ሥልጣናቸዉን ለቀቁ።በምሥራቃዊ አፍጋኒስታን የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት የነበሩት ማቲዉ ሁ እንደሚሉት የአፍቃኒስታን ሸማቂዎች የአሜሪካን ጦር የሚወጉት በርዕዮተ-አለም ወይም በጥላቻ ሳይሆን አሜሪካ ሥለወረረቻቸዉ ነዉ።ሁ የአሜሪካ ወታደሮችም አፍቃኒስታን ዉስጥ የሚሞቱበት በቂ ምክንያት የለም ባይ ናቸዉ።ዩናይትድ ስቴትስ አፍጋኒስታን ዉስጥ የምታኪያሒደዉን ዉጊያ በመቃወም አሜሪካዊ ዲፕሎማት ሥልጣኑን ሲለቅ ሁ የመጀመሪያዉ ናቸዉ።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝሩን ልኮልናል።
አበበ ፈለቀ /ነጋሽ መሀመድ/አርያም ተክሌ