1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ስታድዮም ግንባታ መጓተት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 22 2014

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰን አነጋግረናቸዋል። ለስታድየሙ ግንባታ ምጓተት በተደጋጋሚ የጨረታዎች መሰረዝ፣ ጨረታወን ያሸነፈው  ህንጻ ተቋራጭ በኮቪድ ምክንያት ሰራተኞቹን ማሰማራት አለመቻሉንና የዶላር እጥረትን በምክንያትነት ጠቅሷል

https://p.dw.com/p/451mi
Äthiopien | Stadtansicht Addis Abeba
ምስል Seyoum Getu/DW

የአዲስ አበባ ስታዲየም መጓተት ጥያቄ አስነስቷል።

 

በወንበር 62 ሺ ተመልካቾችን ይይዛል ተበሎ ግንባታው የተጀመረው የአዲስ አበባ ስታድዮም በተያዘለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ ብሔራዊ ቡድኑ በሜዳውና በደጋፊው ፊት ማግኘት ያለበትን ጥቅም አሳጥቶታል ተባለ። አንድ የባህልና ስፖርት  ሚኒስቴር ባለስልጣን አንድ የስፖርት ጋዜጠኛ ለዶቸቨለ እንደተናገሩት የአፍሪካ እግርኳስ ፌደረሽን በኢትዮጵያ ደረጃቸውን የጠበቁ ስታድዮሞች የሉም በማለት አህጉራዊና ቀጣናዊ ውድድሮችን እንዳይካሄዱባቸው እግድ በመጣሉም እግርኳሱን ጎድትታል ብለዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለስታድዮሙ ግንባታ መጓተት የጨረታዎች በተደጋጋሚ መሰረዝ፣ ኮረናና የዶላር እጥረት በምክንያትነት ጠቅሳል። ለረዥም አመታት ሲያግለግል የነበረው ያዲስ አበባ ስታድዮም ከእርጅና ብዛት ውድድሮችን ማካሄድ ወደማይችልበት ደረጃ ደርስል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልል ከተሞች በርካታ ስታድየሞች እየተገነቡ ቢሆንም የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያስቀመጠውን መመዘኛዎችን አንዳቸውም ሊያሟሉ ባለመቻላቸው ካፍ ጨዋታዎች እንዳይካሄድባቸው እገዳ ጥሎባቸዋል።የአገሪቱ የስታድም ችግር ከመቅረፍ በዘለለ የአትሌቲክስ ውድድሮችን ይካሄድበታል ተብሎ በ8 ቢልዮን ብር ግንባታው የተጀመረው የአዲስ አበባ ስታድዮም ይጠናቀቃል ተብሎ ከተያዘለት ጊዜ ለአመታት በመጓተቱ በኢትዮጵያ እግርኳስ እድግት አሉታዊ ጫና እየፈጠረ እንደሆነ የስፖርት ቤተቦች ያማርራሉ።መንሱር አብዱልቀኒ በብስራት ስፖርት የእግር ኳስ ጋዜጠኛና ተንታኝ ባገሪቱ ደርጃቸውን የጠበቁ ስታድየሞች አለመኖራቸውንና የአዲስ አበባ ስታድዮም ግንባታ መጓትት ብራዊ ቡድናችን በሌላ አገር እንዲጫወት በመገደዱ በደጋፊዎቹና በለመደው የአየር ጠባይ ተጫውቶ ማግኘት የነበረበትን ጥቅም እያሳጣው ነው ብሏል።                       

በተለያዩ የክልል ከተሞች ስታድየሞች መገንባታቸውን የሚበረታታ ነው ያለው የስፖርት ጋዜጠኛው መንሱር አንዳቸውም የካፍ መመዘኛ አለማሟላታቸውን እግርኳሱን እንደጎዳው አክሏል።

የአገሪቱ እግር ኳስ መሻሻሎች ቢኖሩትም ወቅቱን የዋጀ አመራር እንዳላገኘም አልሸሸገም። በጉዳዩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰን አነጋግረናቸዋል። ለስታድየሙ ግንባታ ምጓተት በተደጋጋሚ የጨረታዎች መሰረዝ፣ ጨረታወን ያሸነፈው  ህንጻ ተቋራጭ በኮቪድ ምክንያት ሰራተኖቹን ማሰማራት አለመቻሉንና የዶላር እጥረት በምክንያትነት ጠቅሷል።                     

ስታድየሙ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በውቅቱ ባለመጠናቀቁ በእገር ኳሱና በስፖርት ቤተሰቡ እየደረሰ ያለውን ጉዳት አቶ ናስርም ይጋራሉ። በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ፕሮጀክቱን ተዘዋወረው ከጎብኙት በሃላ የነበረበትን የዶላር ችግር እንደተቀረፈለትና ባገርውስጥ ጥሬ እቃዎች የሚከናወኑ ስራዎች ግን እንዳልቋረጡ የገለጹት አቶ ናስር የሚያልቅበት ትክክለኛ ጊዜ ማወቅ እንደማይቻል ገልጿል።

               

ዮሃንስ ገብረእግዚአብህር

ሽዋዬ ለገሰ