የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ7 ጥቅምት 2001ዓርብ፣ ጥቅምት 7 2001በአናት የመጣው የገንዘብ ቀውስ የጉባኤውን ቀልብ ይሳብ እንጂ ከወራት በፊት አስቀድሞ በተያዘው አጀንዳ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመከላከል ከዚህ ቀደም አባላት የተስማሙባቸውን ዝርዝር ነጥቦች ና የአየርላንድ ህዝብ በህዝበ ውሳኔ ውድቅ ያደረገው የተሻሻለው የሊዝበኑ ውል ላይ ለመወያየት ነበርhttps://p.dw.com/p/FcGqየህብረቱ ኮሚሽነር ጆሴ ማኑዌል ባሮሶ እና የወቅቱ የህብረቱ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዞምስል APማስታወቂያ በሀገራቱ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ላይ ተፅዕኖ በማድረግ ውስብስብ ችግሮችን የሚያስከትለው የገንዘብ ቀውስ ዳግም እንዳይከሰት የመከላከያ ዕርምጃው ነበር የጉባኤው ዋነኛ ትኩረት ።