የአውሮፓ ህብረት አምባገነኖችና የ HRW ነቀፌታ
ማክሰኞ፣ ጥር 17 2003ማስታወቂያ
Human rights Watch ትናንት ይፋ ያደረገው እ.ጎ.አ የ 2011 ዓ.ም ዓመታዊ ዘገባው ደግሞ የዚህን ችግር ሌላ ገፅታ ለማሳየት የሞከረ ነው ። ዘገባው በዚህ ዓመት ልዩ ትኩረት የሰጠው የሰብዓዊ መብት በማክበር እና በማስጠበቅ ምሳሌ የሚሆኑ ዓለም ዓቀፍ እና ክፍለ ዓለማዊ ድርጅቶች እንዲሁም ምዕራባውያን መንግስታት ሰብዓዊ መብት የሚጥሱ መንግስታት ላይ ጫና ከማድረግ ይልቅ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በማለፍ ለችግሩ መባባስ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ ላይ ነው ። በዚህ ረገድ HRW የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ፣ የአውሮፓ ህብረትን ፣ ዩናይትድ ስቴትስንና ፈረንሳይን እንዲሁም ጀርመንን በምሳሌነት አንስቷል ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ድርጅቱ በተለይ በአውሮፓ ህብረት ላይ በሰነዘረው ትችት ላይ ያተኩራል ።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ