የአውሮፓ ህብረት ቼክ ሪፐብሊክና ስዊድን
ሐሙስ፣ ሰኔ 25 2001ማስታወቂያ
ስዊድን ሃላፊነቱን የወሰደችው የገንዘብ ቀውስ እና የምጣኔ ሀብት ኪሳራ እንዲሁም ስራ አጥነት አውሮፓን ከመቼውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ በሚፈትንበት ወቅት ነው ። የቼክ ሪፐብሊክ የፕሬዝዳንት ዘመን እንዴት ነበር ? ስዊድንስ ምን ይጠብቃታል ? የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን አንዱ ትኩረት ነው ።
የኢራቅ ስደተኞች በጀርመን
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኢራቅ ስደተኞች ባለፉት ስድስት ዓመታት በተለያዩ ሀገራት የስደት ኑሮ እየገፉ ነው ። ከነዚህም አብዛኛዎቹ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተጠለሉ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ አውሮፓ ደርሰዋል ። የኢራቅን ስደተኞች ካስጠጉት የአውሮፓ አገራት አንዷ ጀርመን ናት ። ከሶሶት ወራት በፊትም ጀርመን በተባበሩት መንግስታት መርሀ ግብር ስር አራት መቶ የኢራቅ ስደተኞችን ተቀብላለች ። የነዚህ ስደተኞች አያያዝ ምን እንደሚመስል የሚያስቃኝ ቅንብርም አለን ።
ሒሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ