የአውሮፓ ህብረት በዚምባብዌ ላይ የጣለው ማዕቀብ
ማክሰኞ፣ ጥር 19 2001ማስታወቂያ
ትናንት ብረሰልስ ቤልጅየም የተሰበሰቡት የህብረቱ አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከከዚህ ቀደሙ ጠንከር ያለ ተጨማሪ የማዕቀብ ውሳኔ ነው ያሳለፉት ። ህብረቱ ከአውሮፓ ኩባንያዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ተጨማሪ የዚምባብዌ ኩባንያዎች ንብረት እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድና ከገዥው መንግስት ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ተጨማሪ ሰዎች ላይ የጉዞ ማዕቀብ የሚጥል ውሳኔ አስተላልፏል ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ልኮልናል ።