የአውሮፓው ኅብረት በኢራን ላይ የአገዳ ውሳኔ ማሳለፉ፣
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2002ማስታወቂያ
ያሁኑ እገዳ፤ በአገሪቱ የኃይል፣ የባንክና የገንዘብ ተቋማት እንዲሁም የንግድና የመገናኛ መሣሪያዎች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ይህም ፤ ኢራን በምታካሂደው የኑክልየር መርኀ-ግብር ሳቢያ እንደሆn ነው የተገለጠው። አሜሪካም እንዲሁ ከአንድ ወር ገደማ በፊት በተመሳሳይ ምክንያት ጥብቅ እገዳ ማስተዋወቋ የሚታወስ ሲሆን፣ ካናዳም ፣ አውሮፓውያን እንዳደረጉት ሁሉ፣ በአገሪቱ የባንክና የኃይል ዘርፎች ላይ ያነጣጠረ እገዳ፣ ያስተዋወቀች መሆኑ ታውቋል። -- ገበያው ንጉሤ--
ተክሌ የኋላ
ሒሩት መለሰ