1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረት የፓርላማ አባላት ምርጫ እና ከፊቱ የተጋረጠው ፈተና

ዓርብ፣ ግንቦት 30 2016

የአውሮጳ ህብረት 27 አባል አገሮች ከትናንት ሐሙስ ጀምሮ የፓርላማ ወኪሎቻቸውን እየመረጡ ነው። አራት ቀናት እንደሚወስድ በሚጠበቀው ምርጫው ከ370 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለመምረጥ ተመዝግቧል። 720 የፓርላማ አባላት በሚመረጡበት ምርጫው ህብረቱ ከሩስያ ዩክሬን ጦርነት እና የስደተኞች ጉዳይ በምርጫው ላይ ተጽዖኖ ሳያሳድር አይቀርም ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4gnOU
Europawahl 2024 | Europa Quartier Brüssel
ምስል Ardan Fuessmann/IMAGO

የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ምርጫ በይፋ ተጀምሯል

አራት ቀናት የሚዘልቀው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ

የአውሮጳ ህብረት 27 አባል አገሮች ከትናንት ጀምሮ እስከ ነገና ከነገ ወዲያ ዕሁድ ድረስ የአውሮፓ ፓርላማ ወኪሎቻቸውን እየመረጡ ነው። ትናንት ኔዘርላንድስ፤ ዛሬ አየርላንድና ቼክ ሪፑብሊክ የመረጡ ሲሆን፤ ነገና ከነገ ውዲያም በቀሩት የህብረቱ አገሮች ምርጫው ይቀጥላል። ከጠቅላላው የህብረቱ 450 ሚሊዮን ህዝብ 370 ሚሊዮኖች  መምረጥ የሚችሉና የተመዘገቡ ሲሆኑ፤ ዘንድሮ የመራጩ ህዝብ ተሳትፎ ከመቺውም ግዜ የላቀ እንደሚሆን ተገምቷል ።። ከ27ቱ አባል አገሮች የሚመረጡ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ቁጥር 720 ሲሆን፤ ከየአገሮቹ የሚመረጡት የፓርላማ አባላት ብዛት  ግን በያገሮቹ የህዝብ ብዛት መጠን የተደለደለ ነው።

የምርጫው ሂደትና በፓርላማው የፖለቲካ ቡድኖች

የፓርላማ አባሎቹ በየአገሮቻቸው በተለያዩ ፓርቲዎች ወይም በግል ተወክለው የሚወዳደሩና የሚመረጡ ቢሆንም፤ ብዙዎቹ በፓርላማው፤ ባውሮፓ ደረጃ በተደራጁ የፖለቲካ ቡድኖች ውስጥ ተካተው ወይም ተደራጅተው ነው የሚሰሩት። የመሀል ቀኙ የክርስቲያን ዴሞክራቶት ፓርቲዎች ስብስብ EPP)፤ የመሀል ግራው የሶሻልና ዴሞክራቶች ስብስብ (S & D)፤  የሊበራሎቹ ቡድን፤ ያረንጉዴዎቹና የግራ ኃይሎች ስብስቦች፤ የወግ አጥባቂዎቹና የማንነትና ዴሞክራሲ ፓርቲዎች ስብስቦች ዋና ዋናዎቹ የፓርላማው የፖለቲካ ስብስቦች ወይም ቡድኖች ናቸው።

ምርጫ አውሮጳ ህብረት 2024
የፓርላማ አባሎቹ በየአገሮቻቸው በተለያዩ ፓርቲዎች ወይም በግል ተወክለው የሚወዳደሩና የሚመረጡ ቢሆንም፤ ብዙዎቹ በፓርላማው፤ ባውሮፓ ደረጃ በተደራጁ የፖለቲካ ቡድኖች ውስጥ ተካተው ወይም ተደራጅተው ነው የሚሰሩት። ምስል Ardan Fuessmann/IMAGO

የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ አዲስ የስደተኞች ሕግ አፀደቀ

የዝነድሮው ምርጫ ልዩ የሆነበት

የዘንድሮው ምርጫ ህብረቱ  በዩክሬን ምክኒያት በተዘዋዋሪም ቢሆን ከሩሲያ ጋር በጦርነት ውስጥ ባለበት፤ የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት የህብረቱ አይነተኛ ፈተና  በሆኑበት፤ የፈላስያንና ስደተኖች ጉዳይ በሰፊው እየተወሳ ባለበትና ከሁሉም በላይ ግን ከዚህ ቀደም ታይቶ ባልታወቀ ሁኒታ በሁሉም የህብረቱ አገሮች በሚባል ደረጃ እራሱን ያውሮፓ ህብረትንም ከጥያቄ ውስጥ የሚያገቡ የቀኝ አክራሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባንሰራሩበትና ባንዳንዶችም መንግስት እስከመሆን  በደረሱበት ወቅት የተካሄደና እየተካሄደ ያለ በመሆኑ ልዩ፤ አጓጊና አሳሳቢም ሁኗል ።

የአክራሪ ብሄረተኞች ድጋፍ ለምን ጭመረ?

የአክራሪ ብሄረተኖችና የህዝበኛ ፓርቲዎች ማደግና ምክኒያቶች በርካታ  ቢሆኑም በለንደን እስኩል ኦፍ ኢኮኖሚስ ፕሮፈሰር ስቲፋኒ ሪካርድ እንደሚሉት ዋናው ምክኒያት ግን  ኢኮኖሚው ነው፡ “ ዋናው ምክኒያት የሚሆነው የኢኮኖሚ ዋስትና ማጣት ነው። መራጩ ህዝብ እያደገ የሚሄደው የዋጋ መናርና የኑሮ ውድነት ያሳስበዋል” በማለት ብሄረተኛና ህዝበኛ ፓርቲዎች ይህን ችግር ድጋፍ ለማገኘት እንደሚጠቀሙበትም አመላክተዋል።

ትኩረት የሳበው የአውሮጳ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ

የምርጫ ዘመቻ አጀንዳዎች

 የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት ፤የአየር ንብረት ለውጥ፤ የስደተኖችና ፈላስያን ጉዳይ፤ የዩክሬኑ ጦርነትና  የአውሮፓ ደህንነት ጉዳዮች ዋናዎቹ የልዩነቶችና  የምርጫ ዘመቻ አጀንዳዎች ናቸው። በዚህ ምርጫ ውጤት የሚመስረተው የፓርላማ አይነት፤ ህብረቱ በነዚህ አጀንዳዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃና የሚከተለውን ፓሊሲ ይወስነዋል።

የአዲሱ ፓርማ የመጀመሪያ ስራና የሚጠበቁ ተግዳሮቶች

 የአዲሱ ፓርላማ የመጀመሪያ ስራ የኮሚሽኑን ፕሬዝድናት መምረጥ ሲሆን፤  ይህም በዲሱ ፓርላማ አዲስ የሀይል አሰላለፍ የሚወሰን ይሆናል።  ትልቁ ፓርቲ  ይሆናል ተብሎ የተገመተው  የመሀል ቀኙ የአውሮፓ ህቦች ፓርቲ (ኢፒፒ)፤ ወይዘሮ ቮንዴር ሌየንን በቀጣይም  የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በዕጩነት ያቀረበ ሲሆን ፤ ይህ ግን ነባር አጋሮች ሆነው ከቆዩት የሶሻሊስቶቹና ሊበራሎቹ የምርጫ ውጤት ጋርም የሚያያዝ ነው። በብዙዎች እንደሚገመተው የወግ አጥባዊቹና የማንነትና ዴሞክራሲ ፓርቲዎች ሁለተኛ ትልቆቹ ፓርቲዎች ከሆኑ፤ ወይዘሮ ቮንዴር ለየን የነሱን ድጋፍ ለማግኘት ከነሱ ጋር በዋናዎቹ የህብረቱ መርሆች ጭምር እንዲደራደሩ ሊገደዱ ይችላሉ ነው የሚባለው። ይህ ከሆነ ደግሞ ያውሮፓ ህብረት ከበርካታ አመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ቀኝ ያደላ መሆኑ የማቀር ነው፤  እንደ ፖለቲካ ታዛቢዎች አስተየየት።

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የድምጽ አሰጣጥ
 የአዲሱ ፓርላማ የመጀመሪያ ስራ የኮሚሽኑን ፕሬዝድናት መምረጥ ሲሆን፤  ይህም በዲሱ ፓርላማ አዲስ የሀይል አሰላለፍ የሚወሰን ይሆናል።ምስል Ramon van Flymen/EPA

የአውሮጳ ሕብረት በስደተኞች ጉዳይ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ

ያዲሱ ፓርላማ ተጠባቂ ችግሮች

የአክራሪና ህዝበኛ ፓርቲዎች ተወካዮች  በፓርላማው በብዛት ከገቡ በህብረቱ ፖሊስዎችና የስራ ሂደት ላይ ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ መሆኑን  በፓርላማው የአውሮፓ ህዝቦች ፓርቲ (ኢፒፒ) ቡድን ፕሬዝዳንት ሚስተር ማንፍሬድ ዌበር ሳይቀር ይናገራሉ፤ “ የመጀመሪያው ነገር እነዚህ ወገኖች ለችግሮች በሚቀርቡ የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ አይስማሙም። ብሄረተኖች መራደርና ሰቶ መቀበል አያውቁም። ሁለተኛ፤ የራሳቸውን ምርት የሚያስቀድሙና የሌላውን የሚከለክሉ ነው የሚሆኑት፡፤ ለምሳሌ ወይዘሮ ለፔን ፕሬዝዳንት ቢሆኑ፤ በፈረንሳይ የፈረንሳይ የምርት ውጤቶች ብቻ ለገበያ እንዲቀርቡ ነው የሚጠይቁት፤ ሼንገንም ችግር ውስጥ ሊገብ ይችላል፤ ለዩዩኪረን በሚሰጠው ድጋፍ ላይም ጥያቄ ሊነሳ ይችላል በማለት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ይዘርዝራሉ ።

የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ

ባጠቃላይም የዘንድሮው ምርጫ ውጤት  የአውሮፓ ህብረት ወደ ቀኝ እንዲያደላ የሚያደርግና ይህም  በህብረቱና አለምቀፍ ጉድዮች ጭምር የፖሊሲ ለወጦች ማስክተሉ የማይቀር እንደሆነ እየተነገረ ነው። ሁሉንም ግን በመጪው ሰኞ ይፋ በሚሆነው የምርጫ ውጤት ለማየት ሁሉም በጉጉትና በጭንቀት ጭምር በመጠባበቅ ላይ  ነው።

ገበያው ንጉሴ

ታምራት ዲንሳ 

ሸዋዬ ለገሰ