የአክባር ሐሼሚ ራፍሳንጃኒ የሕይወት ታሪክ
ሰኞ፣ ጥር 1 2009ማስታወቂያ
ከአገሪቱ መንፈሳዊ መሪ አያቶላኽ አሊኻሚኒ ጋር ጥብቅ ግንኙነት የነበራቸው ራፍሳንጃኒ ኢራን በተፈተነችባቸው አደገኛ ጊዜያት ሁሉ የግንባር ሰው እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከኢራን ቀደምት ባለጠጎች መካከል አንዱ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ሥርዓት ውስጥ የለውጥ ደጋፊ የወግ አጥባቂዎቹ ተቺ የነበሩት አክባር ሐሼሚ ራፍሳንጃኒ ህልፈት ምዕራባውያኑን አሳዝኗል። ራፍሳንጃኒ ግለሰባዊ መብቶች እንዲከበሩ፤ ኢራንም ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ከገባችበት ውጥረት ተላቃ ግንኙነቷን እንድታሻሽል ወትዋች ነበሩ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለሚካኤል የሕይወት ታሪካቸውን የሚዳስስ ዘገባ አጠናቅሮዋል።
ይልማ ሐይለሚካኤል
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ